ልጄ ማመልከት አለበት? (Should my child apply?)
ማመልከቻ ያስገቡ የእርስዎ ልጅ አዲስ ተማሪ የሚሆን ከሆነ በ፥
- በማንኛውም DCPS ትምህርት ቤት የመዋእለህጻናት 3 ወይም መዋእለ ህጻናት 4 ፕሮግራም፣ የእርስዎ የDCPS ወሰን-ውስጥ ትምህርት ቤት እና ማንኛዉም የDCPS የመጀመሪያ ትግበራ ትምህርት ቤት* ጨምሮ
- በማንኛውም የDCPS የወሰን-ውስጥ ትምህርት ቤት (ቅድመመዋዕለህጻናት3 – ክፍል 5) ጥምር-ቋንቋ ክር
- ከወሰንዎ ውጭ የDCPS ትምህርት ቤት ወይም የትምህርት ቤት ቅደም ተከተል፣ በመላው ከተማ ባሉ ትምህርት ቤቶች ያሉ DCPS ጨምሮ (ቅድመ መዋእለ ህጻናት3-ክፍል 12)
- DCPS መራጭ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወይም ፕሮግራም(ከ9-12 ክፍሎች)**
- ተሳታፊ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት (ቅድመ መዋእለ ህጻናት3-ክፍል 12)
እርስዎ ማመልከቻን ማስገባት አያስፈልግዎትም ልጅዎ ቀጥሎ ያሉት ዉስጥ ከሆነ/ች፥
- አሁን ያለው ትምህርት ቤታቸው ውስጥ የሚቆዩ ከሆነ። ለመመዝገብዝም ብለው ትምህርት ቤትዎን ያነጋግሩ።
- የነሱን የDCPS በወሰን ውስጥ ወይም በቅደም ተከተል ባለ ትምህርት ቤት ውስጥ ይመዝገቡ (መዋዕለህጻናት-12 ክፍሎች)
- በህዝብ ቻርተር ቅደም-ተከተል ትምህርት ቤታቸው ያስመዝግቡ (ሁሉም ክፍሎችን)
*"የወሰን ውስጥ ትምህርት ቤት" የDCPS ትምህርት ቤት ሲሆን ተማሪው በቤት አድራሻው መሰረት ከመዋእለህጻናት እስከ 12 ክፍል ድረስ ሊማርበት መብት ያለው ትምህርት ቤት ነው። ተማሪዎች ለመዋእለህጻናት-12 ክፍሎች ድረስ በወሰናቸው ውስጥ ያሉ የእነርሱ DCPS ዉስጥ ለመማር በMy School DC አማካኝነት ማመልከት አያስፈልጋቸውም። የእርስዎ በወሰን-ውስጥ ያሉ የDCPS ትምህርት ቤቶችን ለመለየት ወይም ትምህርት-ቤት-ፈላጊ ውስጥ የቤት አድራሻዎችን ለማስገባት፣ የMy School DC ስልክ መስመር ላይ በ (202) 888-6336 ይደዉሉ። በተሳታፊ DCPS የመጀመሪያ ትግበራ ቅድመመዋእለ ህጻናት ትምህርት ቤት በወሰን ውስጥ የሚኖሩ ተማሪዎች፣ የሚከተሉትን ሁለት ሁኔታዎች እስካሟሉ ድረስ በቅድመመዋእለ ህጻናት 3 ወይም ቅድመመዋእለ ህጻናት 4 ውስጥ ቦታ ለማግኘት ዋስትና ይኖራቸዋል፥ (1) በMy School DC ሎተሪ አማካኝነት እስከ መጋቢት 2፣ 2021 ድረስ ማመልከቻ ካስገቡ እና (1) ማመልከቻቸው ዉስጥ ከፍ ያለ ደረጃ ካስቀመጡት ትምህርት ቤት ጋር ካልተዛመዱ። ለ2022-23 የትምህርት ዓመት የDCPS Early Action PK (ኢርሊ አክሽን ቅድመ መዋእለ ህጻናት) ትምህርት ቤቶችን ለማየት እዚህ ይጫኑ።
**DCPS በተለዩ የመቀበያ መስፈርቶች እና የምርጫ መስፈርቶች መሰረት የተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ፕሮግራሞች አሉት። በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ማንኛውም ሰው ማመልከት ይችላል፣ ነገር ግን የትምህርት ቤቱን መስፈርቶች ያሟሉ ተማሪዎች ብቻ ትምህርት ቤቱ ውስጥ ለመማር ብቁ ይሆናሉ። በአንድ ወይም በብዙ የተመረጡ የDCPS ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወይም ፕሮግራሞች የሚያመለክቱ ተማሪዎች በMy School DC ማማልከቻ ውስጥ ተጨማሪ ክፍል መሙላት አለባቸው። ለበለጠ መረጃ የMy School DC የስልክ መስመርን በ (202) 888-6336 ይደዉሉ።
ሎተሪው እንዴት ይሰራል? (How does the lottery work?)
የMy School DC መደበኛ ሎተሪ በሁሉም ተሳታፊ ትምህርት ቤቶች ያሉ አዲስ ተማሪዎች ምደባን የሚወስን ነጠላ እና የዘፈቀደ ሎተሪ ነው። የተማሪ-ትምህርት ቤት ምደባ በያንዳንዱ ትምህርት ቤት የሚገኙ የቦታዎች ቁጥር፤ ወንድምነት/እህትነት፣ ቅርበት፣ እና ሌሎች የሎተሪ ምርጫዎች፤ እያንዳንዱ ተማሪ የትምህርት ቤት ምርጫቸውን እንዴት ደረጃ እንደሰጡ፤ እና የእያንዳንዱ ተማሪ በዘፈቀደ የሎተሪ ቁጥር ላይ የተመሰረቱ ናቸው። (በMy School DC መደበኛ ሎተሪ በኩል፣ የDCPS የሚመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ፕሮግራሞች ልዩ መስፈርቶች ላይ በመመስረት ተማሪዎችን ቅደም ተከተል ይሰጣሉ።)
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች፥ የልጄ ማመልከቻ ላይ ትምህርት ቤቶችን እንዴት እንደሚደረድር ለምን ችግር አለው?
A: መልስ፥ የሚመለከቱባቸው ትምህርት ቤቶችን እንዴት በደረጃ እንደሚያስቀምጡ ማወቅ በእነዚያ ትምህርት ቤቶች ጋር በምን ቅደም-ተከተል መዛመድ እንደሚፈልጉ ያሳውቀናል። ሎተሪው ተማሪዎችን 1ኛ ምርጫቸው 1ኛ፣ ከዚያ 2ኛ ምርጫቸው፣ ወዘተ እያለ ለመደብ ይሞክራል። ተማሪዎች ከአንድ ትምህርት ቤት የማይበልጥ ጋር ይዛመዳሉ እና የተመደቡበት ትምህርት ቤት በላይ በደረጃ የመደቡ ትምህርት ቤቶች ጋር ብቻ እንደ ተጠባባቂ ይዘረዘራሉ። የማመልከቻ ሂደት ዉስጥ ይህ ደረጃ-ማውጣት ወሳኝ ደረጃ ነው።
እንዴት ማመልከት ይቻላል? (How to Apply)
በአምስት ቀላል ደረጃዎች ማመልከት ይችላሉ። ከ ኦንላይን ማመልከቻ ጋር ለመከታተል እንዲችሉ የማመልከቻ መመሪያዎችን ማዉረድዎን ያረጋግጡ። እንዲሁም በአስተርጓሚ ዕርዳታ ማመልከቻዎን በስልክ ለመሙላት እንዲረዳዎት የMy School DC ስልክ መስመር በ (202) 888-6336፣ ከሰኞ – ዓርብ፣ ጧት 8- ከሰዓት 5 ይገኛል።
ደረጃ 1፥ ዝርዝር ያዉጡ። ለእርስዎ እና ለልጅዎ ከሁሉም አስፈላጊ የሆነ ነገርን ግምት ዉስጥ ያስገቡ፣ የትምህርት ቤት ምርጫዎችዎን ለማጥበብ የትምህርት ቤት ፈላጊን ይጠቀሙ ወይም የMy School DC የስልክ መስመርን ይደዉሉ፣ እና ምን ማቅረብ እንዳለባቸው ለማወቅ ትምህርት ቤቶችን ያግኙ። እነዚህን ጠቃሚ ጥያቄዎችን ይጠይቁ።
ደረጃ 2፥ የMy School DC የቤተሰብ አካውንት እዚህ ይፍጠሩ። ይህን አካውንት ወደ አዲስ ትምህርት ቤት ለሚያመለክት ለእያንዳንዱ ልጅ ማመልከቻ ለማስገባት ይጠቀሙበታል። የኢሜይል አድራሻን ማቅረብ ይኖርቦታል ወይም የ ተጠቃሚ ስም መፍጠር፣ እና የይለፍ-ቃል ማዘጋጀት። አካዉንት ከፈጠሩ በኋላ፣ የመግቢያ መረጃን በደህና ቦታ መፃፍዎን ያረጋግጡ።
ደረጃ 3፥ ለማመልከት የሚፈልጉትን መረጃ ይሰብስቡ።
- የልጅዎ መረጃ፥ ስም፣ የትዉልድ ቀን፣ ያሁኑ ትምህርት ቤት፣ ያሁኑ ክፍል፣ እያመለከቱበት ያሉ ክፍል፣የወንድም/እሂት መረጃ (የሚተገበር ከሆነ)
- የእርስዎ መረጃ (ማለትም፣ ወላጅ ወይም ህጋዊ አሳዳጊ)፥ ስም፣ የመኖሪያ ቤት አድራሻ (ልጁ/ልጅቷ የሚኖርበት/የምትኖርበት አድራሻ ቦታ ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት)፣ የስልክ ቁጥር፣ የሚመርጡ የመነጋገሪያ ቋንቋ*
- *የMy School DC ማመልከቻ ለአሳዳጊ ተመራጭ ቋንቋን ይጠይቃል፣የMy School DC ቡድን ከአሳዳጊ ጋር በተሻለ ሁኔታ መነጋገር እንዲችሉ። አርሱለ ተማሪዎች ምደባ አይጠቅምም እና በየትኛዉም መንገድ የሎተሪ ዉጤት ላይ ተጽኖ አይፈጥርም።
ደረጃ 4፥ የልጅዎን ማመልከቻ የቤተሰብዎ አካዉንት ዉስጥ ይጀምሩ።
- የልጅን መረጃ እና የአሳዳጊ መረጃን ያስገቡ። የደረጃ በደረጃ ሂደትን እዚህ ይከታተሉ።
- ማመልከት የሚፈልጉባቸውን የትምህርት ቤቶች ዝርዝር ያስገቡ።እስከ 12 ትምህርት ቤቶች ጋ ማመልከት
- ከሁሉም በተሻለ በሚወዱት ቅደም ተከተል ደረጃ ስጡአቸው። 1ኛ ምርጫዎን (በጣም የሚፈልጉትን ትምህርት ቤት)፣ ከዚያ 2ኛምርጫ፣ እና ወዘተ እያሉ ይዘርዝሩ።
- ሁሉም በትክክል እንደገባ ለማረጋገጥ መረጃዎን ይገምግሙ።
ደረጃ 5፥ የልጅዎን ማመልከቻን በመጨረሻ የጊዜ ገደብ ያስገቡ፥ የካቲት 1 (9-12 ክፍሎች)፣ መጋቢት 1 (ቅድመ መዋእለ ህጻናት 3 – ክፍል 8)
- ማመልከቻዎን ለማስተካከል ከመጨረሻ ቀነ-ገደብ በፊት በየትኛዉም ጊዜ በቤተሰብ አካዉንትዎ ዉስጥ መግባት ይችላሉ።
ለመመዝገብ (How to Enroll)
ልጅዎ በሎተሪ በኩል ከትምህርት ቤት ጋር ከተዛመደ/ች፣ በትምህርት ቤቱ የመጠባበቂያ ዝርዝር ዉስጥ ግብዣ ከተቀበሉ፣ ወይም ከሎተሪ-በኋላ ካመለከቱ እና እርስዎ ካመለከቱት ትምህርት ቤት ልጅዎ ቦታ እንዲያገኝ/እንዲታገኝ ግብዣ ከቀረበ፣ የልጁ/ልጅቷ ወላጅ ወይም አሳዳጊ ልጁን/ልጅቷን በአዲሱ ትምህርት ቤታቸው ለማስመዝገብ ሦስት ደረጃዎችን መከተል አለባቸው፥
- የ DC ነዋሪነትን ማረጋገጥ፤
- ሁሉም የትምህርት ቤቱን የምዝገባ መስፈርቶችን ያሟሉ።
- ወቅታዊ የጤና ቅጾችን ያስገቡ።
ልጆችዎ ከትምህርት ቤት ጋር በሎተሪ አማካኝነት የተዛመዱ ከሆነ፣ በተለመደው የመመዝገቢያ የመጨረሻ ቀን ማስመዝገብ እንዳለብዎ ያስታዉሱ። በተዛመዱበት ትምህርት ቤት ልጅዎን ማስመዝገብ ልጅዎን ከሌሎች ትምህርት ቤቶች የተጠባባቂ ዝርዝር እንዲሰረዝ አያደርገውም። ስለ እንዴት እንደሚመዘገብ ጥያቄዎች ትምህርት ቤትዎን ያግኙ።
የተጠባባቂ ዝርዝሮች እንዴት ይሰራሉ? (How do Waitlists Work?)
ልጅዎ በትምህርት ቤት የተጠባባቂ ዝርዝር ላይ ከሆነ፣ በቤተሰብዎ አካውንት ውስጥ በመግባት በማናቸውም ጊዜ የተጠባባቂ ዝርዝር ላይ ያሎትን ሁኔታ መመልከት ይችላሉ። በማንኛውም ትምህርት ቤት የተደረጉ የተጠባባቂ ዝርዝር ማሻሻያዎች ሲገቡ ወዲያው አካዉንትዎ ዉስጥ ይታያሉ።
ይህ እንዴት እንደሚሰራ ነው፥
- ልጅዎ በትምህርት ቤቱ የቀረበዉን የተጠባባቂ ዝርዝር ካራዘመ/ች፣ ለዛዉ የተለየ ትምህርት ቤት የልጅዎ ሁኔታ "የተጠባባቂ ዝርዝር ግብዣ ተራዝሟል (ምዝገባዉ ተይዞ ቆይቷል)" ለማሳየት ይቀየራል። በMy School DC የቀረበ አዲስ ግብዣ በኢሜይል (የኢሜይል አድራሻን አቅርበው ከሆነ) እና በፅሁፍ (ማስታወቂያን በሞባይል ስልክዎ በኩል ለመቀበል መርጠው ከሆነ) በአፋጣኝ እንዲያዉቁ ይደረጋሉ። በተጨማሪም ትምህርት ቤቱ በስልክ ያገኘዎታል። My School DC እና ትምህርት ቤቱ የትምህርት ቤቱን የምደባ ግብዣን መቀበል ያለብዎትን የቀናት ቁጥር ያሳልፋሉ።
- በተነጋገረው ቀነ-ገደብ ለትምህርት ቤቱ መልስ ካልሰጡ፣ ትምህርት ቤቱ ልጅዎን ለማስመዝገብ ፍላጎት እንደሌሎት ያስባል እና በእርስዎ ፋንታ ቦታዉን ዉድቅ ያደርጋል። የመጨረሻ ቀነ-ገደባቸውን ለመሙላት ሀሳብ ከገባዎት እባክዎ በአፋጣኝ ትምህርት ቤቱን ያግኙ።
- በትምህርት ቤቱ የቀረበው የተጠባባቂ ዝርዝር ለመቀበል፣ ወላጅ ወይም ህጋዊ ሞግዚት የሚያስፈልገውን ሁሉንም የመመዝገቢያ ሰነዶች ለትምህርት ቤቱ ማስገባት አለባቸው። የምዝገባ እና የመኖርያ ማረጋገጫ ሂደቶቻቸውን ለማወቅ ትምህርት ቤቱን ያግኙ። አንድ ጊዜ ከተመዘገቡ በኋላ፣ ልጅዎ በማመልከቻዎ ላይ ከተመዘገበበት ትምህርት ቤት በታች ካሉት ሁሉም የተጠባባቂ ደረጃ ፣ እንዲሁም አሁን እሱ ወይም እሷ ከተመዘገቡበት ሁሉም ትምህርት ቤቶች ይሰረዛል/ትሰረዛለች።
የሎተሪ ማመልከቻ የመጨረሻ የጊዜ ገደቦች አለፉዎት? (Missed the lottery application deadlines?)
አሁንም ለህዝብ ትምህርት ቤቶች ማመልከት ይችላሉ! የሎተሪ ማመልከቻ የመጨረሻ የጊዜ ገደብ ያለፈባቸው ቤተሰቦች የMy School DC መተግበሪያን በመጠቀም ወደ ትምህርት ቤቶች ማመልከት ይችላሉ። ይህ ማመልከቻ ድህረ-ሎተሪ ማመልከቻ ተደርጎ ይቆጠራል። የMy School DC ድህረ-ሎተሪ የማመልከቻ ጊዜ የሚጀምረው ለ9-12 ክፍል አመልካቾች የካቲት 2፣ እና ለሁሉም ክፍሎች ደግሞ መጋቢት 2 ነው።
በድህረ-ሎተሪ የማመልከቻ ጊዜ የሚያመለክቱ አመልካቾች፣ ማመልከቻቸውን በሚያስገቡበት ጊዜ ወዲያዉኑ የትምህርት ቤት የመጠባበቂያ ዝርዝር ዉስጥ ይጨመራሉ እና እስከ ሎተሪ የመጨረሻ ቀነ-ገደብ ያመለከቱ የመጠባበቂያ ዝርዝር ዉስጥ የገቡ አመልካቾች በታች ይቀመጣሉ። ለዚህ ብቸኛዉ ቀሪ በትምህርት ቤት ለሎተሪ ተመራጭ ብቁ ለሆኑ አመልካቾች ነው፣እንደ በወሰን-ዉስጥ ወይም ወንድም/እሂት ያለ፣የተጠባባቂ ዝርዝር ዉስጥ የገቡ የሎተሪ አመልካቾች ብቁ የማይሆኑለት። ለምሳሌ፣ ወንድም/እህት ምርጫ ያለው የድህረ-ሎተሪ አመልካች በመጠባበቂያ ዝርዝር ላይ የወንድም/እህት ምርጫ ከሌለው አመልካች ጋር ሲነጻጸር ከፍ ብሎ ይቀመጣል።
ጥያቄዎች? የ My School DC ማመልከቻ ማስገባት ላይ ድጋፍ ይፈልጋሉ? (Questions? Need assistance completing the My School DC application?)
የMy School DC የስልክ መስመር ጋር በ(202) 888-6336፣ ከሰኞ-አርብ፣ ከ8 ጧት-5 ከሰዓት ድረስ ይደውሉ ወይም በ
[email protected] ኢሜይል ይላኩልን። የ My School DC ተወካይ ከአስተርጓሚዎ ጋር በመሆን ሊረዳዎ ዝግጁ ነው። እርስዎን በደስታ ተቀብለን ለመርዳት እኛም ዝግጁ ነን።